የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ብሎ ያስተላለፈው ደብዳቤ ማነጋገሩን ቀጥሏል
TRACK

የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ብሎ ያስተላለፈው ደብዳቤ ማነጋገሩን ቀጥሏል

00:00

መስከረም 21፣2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ከ15 ቀናት በፊት ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ብሎ ያስተላለፈው ደብዳቤ ግርታም፣ የግንባታ መቀዛቀዝም፣ በምንድነው ነገርነቱም ማነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ደብዳቤው ህንፃ ከመንገድ መራቅ ያለባቸውን ርቀት (setback)፣ የመሬት ስፋት ዝቅተኛ ገደብ እና የህንፃ የጎን ስፋት የሚመለከት ነው፡፡

በዚህም ህንፃ ከመንገድ መራቅ ያለባቸው 10፣ 5፣ 3 እና 2 ሜትር እንዲጠበቅ፣ በ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት(sefback) ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበት እንዲሁም ዝቅተኛው የህንፃ የጎን ስፋት በ20 ሜትር ያላነሰ መሆን እንደሚገባው ያስረዳል፡፡

እነዚህም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ሆነ በኮሪደር ልማት ክልል ውጪ ጭምር በከተማ አስተዳደር ወሰን ውስጥ በሙሉ ተፈፃሚ እንደሚሆንም በደብዳቤው ተጠቅሷል፡፡

የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ይህ ጉዳይ ሰኔ 2016 ዓ.ም በከተማ ካቢኔ የፀደቀ መሆኑንን ጠቅሷል፡፡

ሆኖም ውሳኔው ተግባራዊ እንዲደረግ በሰርኩላር ቢተላለፍም በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና ባለሞያዎች ህጉን እያጣሱት መሆኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ ተናግሯል፡፡

Comments

00:00