በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ 47 የግል ትምህርት ቤቶች ተዘጉ፡፡
TRACK

በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ 47 የግል ትምህርት ቤቶች ተዘጉ፡፡

Avatar

ጥቅምት 15፣2017

በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ 47 የግል ትምህርት ቤቶች ተዘጉ፡፡

ከተዘጉት በተጨማሪ ሌሎች 60 ትምህርት ቤቶችም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

የትምህርት ጥራት አለማሟላት፣ ህብረተሰቡን ያላማከለ ክፍያ አለማስከፈል፣ ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ እና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ካደረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በሸገር ከተማ 1,156 ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን 855ቱ የግል ትምህርት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ከነዚህ ውስጥ 60 ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው 47 ትምህርት ቤቶች ደግሞ እንዲዘጉ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar