አዲስ አበባ ውስጥ ከቤቶች ጋር ተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት የጉቦ ጥያቄና ሲስተም የለም የሚል ምላሽ እየተሰጠን ተቸግረናል ሲሉ ተገልጋዮች ቅሬታቸውን አቀረቡ
TRACK

አዲስ አበባ ውስጥ ከቤቶች ጋር ተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት የጉቦ ጥያቄና ሲስተም የለም የሚል ምላሽ እየተሰጠን ተቸግረናል ሲሉ ተገልጋዮች ቅሬታቸውን አቀረቡ

Avatar

ሚያዝያ 30 2017

አዲስ አበባ ውስጥ ከቤቶች ጋር ተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት የጉቦ ጥያቄና ሲስተም የለም የሚል ምላሽ እየተሰጠን ተቸግረናል ሲሉ ተገልጋዮች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

በሸገር አንዳንድ ነገሮች ዝግጅት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ተገልጋዮች ከተማ አስተዳደሩ ስር ወዳሉ ክፍለ ከተማዎች እና ወረዳዎች ከመሬት ጋር የተያያዘ አገልግሎቶች ለማግኘት እየተቸገርን ነው ብለዋል፡፡

በ15 እና 20 ቀን ማለቅ የነበረበት ጉዳይ በዚህ ምክንያት በወራቶች ውስጥ አይፈፀምልንም ያሉት ሀሳባቸውን ያጋሩ የከተማው ነዋሪዎች በዚህም ምክንያት ለእንግልት እየተዳረግን ነው ይላሉ፡፡

ተስፋዬ ገብረሚካኤል የተባሉ ነዋሪ በተደጋጋሚ ዲጂታል ካርታ ለማግኘት ክፍለ ከተማ ቢሄዱም እስካሁን ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar