በሀገሪቱ ሰላም እንዲወርድም ‘’በመጀመሪያ መኖሪያችሁ በሆነው ማህጸናችን፤ በመጀመሪያ ምግባችሁ በሆነው ጡታችን’’ በማለት ተማጽነዋል፡፡
TRACK

በሀገሪቱ ሰላም እንዲወርድም ‘’በመጀመሪያ መኖሪያችሁ በሆነው ማህጸናችን፤ በመጀመሪያ ምግባችሁ በሆነው ጡታችን’’ በማለት ተማጽነዋል፡፡

Avatar

የካቲት 11 2017

በኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀው የሰላም እጦት እና የንፁን ሞት አስጨንቆናል በማለት፤ የተለያዩ አካላት ለመንግስት እና በተቃርኖው ለቆሙት የሰላም አውርዱ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

በተለያዩ መድረኮች የሰላም ጥሪ ከሚያቀርቡት መካከል ‘’የገዳይም የሟችም እናት እኔው ነኝ’’ በማለት የሚታወቁት የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ማህበር አንዱ ነው፡፡

እነዚህ እናቶች የሰሜኑ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ወደ መቀሌ ሄደው ‘’እርቅ ይውረድ’’ ብለው ተማጽነው እንደነበረም ይታወቃል፡፡

የእናቶች ማህበሩ ለዓመታት ያደረኩት የሰላጥሪ በሚፈለገው ልክ ውጤት ባያመጣም አሁንም ለመንግስትም ሆነ ለታጣቂዎች የሰላም ጥሪ ማቅረቤን አላቆምም፤ ተስፋም አልቆርጥም ሲል ነግሮናል፡፡

በሀገሪቱ ሰላም እንዲወርድም ‘’በመጀመሪያ መኖሪያችሁ በሆነው ማህጸናችን፤ በመጀመሪያ ምግባችሁ በሆነው ጡታችን’’ በማለት ተማጽነዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሰላም እናቶች ተወካይ ወ/ሮ መዓዛ በቀለ ‘’በ1997 ዓ.ም የነበረው ሁኔታ አስገድዶን የጀመርነው የሰላም ጥሪ ዛሬም ቀጥለናል’’ ብለውናል፡፡

Comments

Avatar