የምግብ ዘይት ችግር አንድ አማራጭ የሚሆን የምርመራ ውጤት የኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩ ተመራማሪዎች እንካችሁ ብለዋል፡፡
TRACK

የምግብ ዘይት ችግር አንድ አማራጭ የሚሆን የምርመራ ውጤት የኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩ ተመራማሪዎች እንካችሁ ብለዋል፡፡

Avatar

ግንቦት 27 2017

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከውጭ ሀገር ለምታስገባው የምግብ ዘይት ከ650 ሚሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች፡፡

ዘይት አንዳንዴ ከ #ቀረጥ_ነፃ አንዲገባ ሲፈቀድ፣ ከገበያ ሲጠፋ፣ ዋጋው ሲሰቀል በተደጋጋሚ ያጋጥማል፡፡

ለዚህ የምግብ ዘይት ችግር አንድ አማራጭ የሚሆን የምርመራ ውጤት የኢትዮጵያ ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩ ተመራማሪዎች እንካችሁ ብለዋል፡፡

ምርምሩ በእጅ በሚሰራ አነስተኛ ማሽን ከ #አቮካዶ የምግብ ዘይት ማምረት ነው፡፡

ምርምሩን በውጤት እስኪታጀብ 3 ዓመታት መውሰዱን በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተማራማሪ እና የምርመራ ስራው አባል እዩቤል ሙሉጌታ ነግረውናል፡፡

አቮካዶ አምራች ገበሬዎች በየሰፈራቸው ተደራጅተው ከቁርጥራጭ ብረቶች በተሰራችና 50,000 ብር በምታወጣ ማሽን የምግብ ዘይት የማምረት ምርምር አመርቂ ውጤት አምጥቷል ተብሏል፡፡

በዚህም ከ100 ኪ.ግ የአቮካዶ ፍሬ 8 ሊትር ዘይት ማግኘት ችለናል ሲሉ ተመራማሪው አስረድተዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1

📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar