በኢትዮጵያ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለበትን ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ሃገራዊ ጥናት እየተከወነ ነው፡፡
TRACK

በኢትዮጵያ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለበትን ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ሃገራዊ ጥናት እየተከወነ ነው፡፡

Avatar

ግንቦት 2 2017

በኢትዮጵያ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለበትን ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ሃገራዊ ጥናት እየተከወነ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል የሚከወነው ይኸው ጥናት ፅኑ የአእምሮ ህመም ሲከሰት ቤተሰቦች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድነው፤ህመሙ ሲከሰት ሰዎች መፍትሄ ለማግኘት ወደየት መሄድን ይመርጣሉ፤

የሚለውና ሌሎችም ጉዳዮች የትኩረት ማዕከል ሆነው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በተመረጡ አካባቢዎች ጥናቱ እየተከወነ መሆኑን ስራውን በበላይነት የሚመሩትና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል ፕሮፍሰር የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አለም ነግረውናል፡፡

Comments

Avatar