የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው  ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ።
TRACK

የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ።

00:00

ህዳር 5 2018

በተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ የሚደረገው ክትትል እንደሚጠናከር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናገረ።

ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ ድብደባ የፈጸመ አንድ የውጪ ዜጋ እና የቅርብ ሃላፊው የስራ ውላቸው ተቋርጦ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉን ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ ተናግሯል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸው ተከብሮ እየሰሩ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ፤ የሚደረገው ክትትል በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተናግሯል።

ኮርፖሬሽኑ ከሠሞኑ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአንድ ኢትዮጵያዊ ሠራተኛ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት መነሻ አድርጎ እንዳለው የትኛውም ስራ ሲሰራ የዜጎችን መብት ባከበረ መልኩ መሆን አለበት።

Comments

00:00