የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ እንቅስቃሴ አለመዘመን ሀገሪቱ በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል ገቢ እና ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓታል ተባለ
TRACK

የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ እንቅስቃሴ አለመዘመን ሀገሪቱ በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል ገቢ እና ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓታል ተባለ

Avatar

ህዳር 6፣ 2017

የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ እንቅስቃሴ አለመዘመን ሀገሪቱ በዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ያህል ገቢ እና ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓታል ተባለ።

በዘርፉ ላይ ያለው የክትትል እና ቁጥጥር ስርዓቱም ደካማ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንን ችግር ይፈታል የተባለለት ስምምነትም በኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን እና በባዝራ ሞተርስ መካከል ተፈርሟል።

ስምምነቱም በሎጀስቲክስ ዘርፍ ላይ ያለውን ኋላቀር ነው፤ የተባለውን አሰራር ለማዘመን በጋራ ለመስራት መሆኑን ሰምተናል፡፡

የባዝራ ሞተርስ ዋና ስራ አስኪያጅ ያየህይራድ አስናቀ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በተለይ በሎጀስቲክስ ዘርፍ የምትከተለው የአሰራር ስርዓት አለመዘመን፣ ክትትልና ቁጥጥር አለመኖር፣ የደላሎች ሰንሰለት በአሰራር ስርአት ውስጥ መኖርና እና መሰል የአሠራር ክፍተቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ መጠቀም የሚገባትን ያህል እንዳትጠቀም ትልቅ ማነቆ መሆኑን ተናግረዋል።

Comments

Avatar