ከታጣቂው ሸኔ ጋር ከተካሄደው ድርድር ‘’የተገኘ ስኬት ባለመኖሩ መንግስት ለህዝቡ ምንም ማለት አልቻለም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
TRACK

ከታጣቂው ሸኔ ጋር ከተካሄደው ድርድር ‘’የተገኘ ስኬት ባለመኖሩ መንግስት ለህዝቡ ምንም ማለት አልቻለም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ

Avatar

ጥር  28፣2016

ከታጣቂው ሸኔ ጋር በታንዛንያ ከተካሄደው ድርድር ‘’የተገኘ ስኬት ባለመኖሩ መንግስት ለህዝቡ ምንም ማለት አልቻለም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ቡድኑ ከ5 ዓመት በፊት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከሌሎች ሃይሎች በተለየ የተሰጠው ቃልም የለም ብለዋል ።

ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በነበረው ውይይት ላይ ከተነሱ ጉዳዮች አንዱ ከሸኔ ጋር የተካሄደው ድርድር እና ድርድሩ ያልተሳካበትን ምክንያት የተመለከተ ነው።

‘’መንግስት በቀጣይ ከቡድኑ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ምን አስቧል?’’ ሲሉ ጉዳዩን ያነሱ የምክር ቤት አባል ጠይቀዋል።

ከሸኔ ጋር ባለው ጉዳይ የሚነሳው አንዱ ጥያቄ ‘’ቡድኑ ምን ቃል ተገብቶለት ነው ከ5 ዓመት በፊት ወደ ሀገር ውስጥ የገባው? ምንስ ሳይፈጸምለት ቀርቶ ነው ወደ ግጭት ያመራው’’ የሚል እንደሆነ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው፤ ጥያቄው ግን ‘’ነገሩን በሴራ አይን ከመመልከት የመጣ ነው’’ ሲሉ አክለዋል።

መንግስት ከቡድኑ ጋር በታንዛንያ ድርድር እንደሚያካሂድ በጊዜው ለህዝቡ ይፋ ማድረጉን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘’በነበሩ ውይይቶች ግን ይህን አሳካን ብለን ለህዝቡ የምንነግረው ድምዳሜ ላይ ባለመደረሱ  ምንም ማለት አልቻልንም’’ ብለዋል።

#Ethiopia #ShegerWerewoch  #ታጣቂ_ቡድን #ሸኔ #ታንዛንያው_ድርድር #ፓርላማ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:  https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar