የአፍሪካ ቀን ብሄራዊ በዓል እንዲሆን በድጋሚ ተጠየቀ
TRACK

የአፍሪካ ቀን ብሄራዊ በዓል እንዲሆን በድጋሚ ተጠየቀ

Avatar

ግንቦት 14 2017

የአፍሪካ ቀን ብሄራዊ በዓል እንዲሆን በድጋሚ ተጠየቀ፡፡

የዛሬ 62 ዓመታት በ1955 ዓ.ም ነበር በቀድሞ አጠራር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተው፡፡

የህብረቱ የምስረታ ቀን የሆነውን ሜይ 25 ወይም ግንቦት 16 የአፍሪካ ቀን ሆኖ ሲከበር ቆይቷል፡፡

የዘንድሮውም የፊታችን እሁድ ግንቦት 16 ቀን ለ62ኛ ጊዜ ይከበራል፡፡

ቀኑን ለተከታታይ ዓመታት ሲያከብር የቆየው አፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ የተባለው የሲቪል ማህበተሰብ ድርጅት ቀኑ በኢትዮጵያ ብሄራዊ በዓል እንዲሆን ለመንግስት አካላት ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ እንዳላገኘና መጠየቁን እንደሚቀጥል ነግሮናል፡፡

Comments

Avatar