ነሀሴ 16 2017
ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ከደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች ማስወገዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ተናገረ፡፡
ይህንን ችግር ፈጥረዋል ያላቸውን ከ2,000 በላይ ድርጅቶች መቅጣቱንም ሰምተናል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን ያለው በዛሬው እለት የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል ያላቸውን ሰራተኞቹን በሸለመበት እንዲሁም ለአገልግሎት አመቺ እንዲሆን በሚል ለሰራተኞቹ ያዘጋጀውን የደምብ ልብስ ባስተዋወቀበት ወቅት ነው፡፡
ለማህበረሰቡ የሚቀርበውን ምግብና መድሃኒት ደህንነቱን የሚቆጣጠረው ባለስልጣኑ ባለፈው የ2017 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ በአቀማመጥ በአመራረትና በሽያጭ ወቅት በምግብና መጠጦች ጥራትና ደህንነት ላይ የጥራት ጉድለት ፈጥረዋል ባላቸው ከ2 ሺህ 49 በላይ ድርጅቶች ላይ ከገንዘብ ቅጣት ለህግ እስከ ማቅረብ የደረሰ እርምጃ መውሰዱን ተናግሯል፡፡
በዚህም ከእነዚህ ድርጅቶች የተሰበሰቡ 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ምግብ ነክ ምርቶች መወገዳቸውን የነገሩን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ ናቸው፡፡
Comments