የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ መውጫ በሮች ላይ ድንገተኛ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ ጉዳይ
TRACK

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በቅርቡ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ መውጫ በሮች ላይ ድንገተኛ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ ጉዳይ

Avatar

ጳጉሜ 5 2017

በቅርቡ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ብቃት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ እና ዙሪያ መውጫ ብሮች ላይ ድንገተኛ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ አድርጓል፡፡

ይህም በተለይ አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከከተማ ለማስወጣት የተደረገ ነው በሚል ቅሬታ ሲቀርብ ነበር፡፡

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ የቴክኒክ ብቃት ፍተሻው የተደረገው ከደህንነት አንፃር እንጂ ሌላ ዓላማ ኖሮት አይደለም ብሏል፡፡

በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሃዲስ በተሽከርካሪዎች ላይ ያደረግነው ክትትልና ድጋፍ የተካሄደው ተሽከርካሪዎችን የእድሜ ዘመን በመመልከት ከሚደርስ አደጋ እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹ በቂ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ስለማድረጋቸው ለማረጋገጥ እንጂ ሌላ ዓላማ ኖሮት አይደለም ብለዋል፡፡

Comments

Avatar