ሰኔ 20 2017
በኢትዮጵያ የባንክ ገበያ መሳተፍ የሚፈልጉ የውጭ ባንኮች ከትናንት ጀምሮ ማመልቻቸውን ለብሔራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
ባንኮቹ የኢትዮጵያን ገበያ ሲቀላቀሉ ማሟላት ያለባቸውን ዝርዝር መስፈርት የያዘ መመሪያም ይፋ ሆኗል፡፡
ከ30 በላይ ባንኮች ቢኖሩም ሀብታቸው 1 ቢሊየን የደረሱት 4ቱ ብቻ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ባንኮች ተፎካካሪ ለመሆን ምን ይጠበቅባቸዋል?
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፕራግማ ካፒታል መስራች እና የኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ባለሞያው መርዕድ ፍቅረ ዮሀንስ ባለፉት 30 አመታት የነበረው ፖሊሲ 30 ትናንሽ ባንኮች እንዲፈጠሩ አድርጓል ይላሉ፡፡
ከግል ባንኮች መካከል 100 እና 200 ሚሊየን ዶላር ብድር ቢጠየቅ የሚሰጥ አለ ወይ? ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡
ከነበረው የፖሊሲ ችግር ባሻገር ባንኮች የገንዘብን እሳቤ ትተው በብሔር እና በሃይማኖት በመቧደን የሚሰሩ መሆናቸው ሌላው ችግር ነው ብለዋል፡፡
Comments