የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ በኋላ ለባቡር ሾፌርነትና ቴክኒሺያኖች ስልጠና ማረጋገጫ ወደ ቻይና አልሄድም አለ
TRACK

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ በኋላ ለባቡር ሾፌርነትና ቴክኒሺያኖች ስልጠና ማረጋገጫ ወደ ቻይና አልሄድም አለ

00:00

ነሀሴ 28 2017

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ በኋላ ለባቡር ሾፌርነትና ቴክኒሺያኖች ስልጠና ማረጋገጫ ወደ ቻይና አልሄድም አለ፡፡

ምድር ባቡሩ ከዚህ ቀደም ለቻይና የባቡር ቴክንሺያኖችና የሰው ሀይል ስልጠና በ6 አመት ውስጥ ብቻ 357 ሚሊዮን ዶላር አውጥቻለሁ ፤ አሁን ግን በሀገር ቤት የብቃት ማረጋገጫ መስጠት የሚያስችለኝን አሰራር ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ለባቡር ሾፌሮ ፤ ኦፕሬሽን ፤ ስልጠና እና ጥገና እንዲሁም አጠቃላይ ባቡሩ ውሎ እስኪያድርበት ላለው ጉዞ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚቀረጥፍብኝን አሰራርን አስቀርቻለሁ ብሏል።

ምድር ባቡሩ ይህን አገልግሎት መጀመሬ ከዚህ ቀደም ከቻይና ለሚመጡና ይህንኑ ተግባር ላከናወኑ ቡድኖች ከ350 ሚሊየን ዶላር በላይ ማውጣቴን ያስቀርልኛል ብሏል።

Comments

00:00

Habtezena

አንዴት ነው መመዝገብ የሚቻለው

There is no more content to load