TRACK
በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቢወሰን የኑሮ ውድነቱ ይበልጥ ተባብሶ ተቀጣሪ የሆነው ሠራተኛ የባሰ ሊጎዳ ይችላል የሚሉ ስጋቶች ይደመጣሉ
ሐምሌ 18 2017
በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ቢወሰን የኑሮ ውድነቱ ይበልጥ ተባብሶ ተቀጣሪ የሆነው ሠራተኛ የባሰ ሊጎዳ ይችላል የሚሉ ስጋቶች ይደመጣሉ።
መንግስት በበኩሉ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን መወሰን ተገቢ ቢሆንም ሌሎች ሀገራት የሰሩትን ስህተት ላለመድገምም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።
በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ ግን ሁለቱንም ስጋቶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ የደመወዝ ወለሉን ማስቀመጥ ይቻላል ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የደመወዝ ቦርድ የሚያቋቁመውን አዋጅ ካፀደቀች ስድስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ዛሬም ግን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን አልወሰነችም።
Comments