ሰኔ 24 2017
#ምጣኔ_ሐብት
ሀገሮች የማክሮ ኢኮኖሚያቸው ሲታመም ወይም ሲንጋደድ ወይም አጠቃላይ ብሔራዊ ምጣኔ ሐብታቸው ሲረበሽ ምን ያደርጋሉ?
ለዘመናት የሚጓዙበትን መንገድ በመፈተሽ ቀድመው ከሚተገብሩት ጠንካራ የማክሮ ኢኮኖሚ መሳሪያ አንደኛው እና ዋነኛው የብር ወይም የገንዘባቸውን ዋጋ በማዳከም በገበያው እንዲወሰን ማድረግ ነው።
ይህ ሀሳብ ወይም መሳሪያ በሀገሮቹ ብሔራዊ ጉዳዮች ብቻ የሚወሰን አይደለም።
እንደውም የምዕራባውያኖቹ ጫናም አለበት ተብሎ ይተቻል፤ በእርግጥ ይህ ሀሳብ እራሱ በባለሞያዎቹ ለሁለት ይከፈላል።
የሚስማሙበትም አሉ የማይስማሙበትም ባለሞያዎች ሀሳብ ይሰማል።
Comments