TRACK
በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አማካይነት የተዘጋጀ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም ኮንፈረንስ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይካሄዳል ተባለ
ነሀሴ 16 2017
በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አማካይነት የተዘጋጀ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰላም ኮንፈረንስ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይካሄዳል ተባለ፡፡
ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በፌዴራል ደረጃ ኮንፈረንሱ ይካሄዳል ተብሏል፡፡
የቤት ስራ የሚሰጣቸው ተቋማት ይኖራሉ፤ በክትትልም የተሰጡ ስራዎች ከምን ደረሱ? በሚል ይገመገማሉ መሳተፍ የሚችሉ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉም ጥሪ ይደረጋል ሲሉ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ እድሮችን የመሳሰሉ የማህበረሰብ ተቋማት በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ እንዲሳተፉ ከተደረገ የሚፈለገው ሰላም መምጣት ይችላልም ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
Comments