ኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል ብቻ እንዲሆን ወስና፤ ወደ ስራ ከተገባ 2 ዓመት ሞልቷል፡፡
TRACK

ኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል ብቻ እንዲሆን ወስና፤ ወደ ስራ ከተገባ 2 ዓመት ሞልቷል፡፡

Avatar

ነሀሴ 7 2017

ኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል ብቻ እንዲሆን ወስና፤ ወደ ስራ ከተገባ 2 ዓመት ሞልቷል፡፡

ይህም የተደረገውም የነደጅ መደበቅ፣ ከተመን በላይ መስከፈል እና መሰል በዘርፉ ይታዩ የነበረው ችግሮችን ያስቀራል በሚል እንደሆነ በመንግስት በኩል ተነግሮ ነበረ፡፡

አዲሱ አሰራር በተጀመረበት 2015 የመጨረሻዎቹ ወራት በአተገባበሩ ወቅት የገጠሙ ችግሮችም ነበሩ፡፡

ተጠቃሚዎች ለአሰራሩ አዲስ መሆናቸው፣ የሲስሙ ተደራሽ አለመሆን፣ የሚተገበርበት ስርዓት ጥቂት ብቻ መሆን በወቅቱ ከገጠሙ ችግሮች የሚጠቀሱ ነበሩ፡፡ በዚህም በየነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም ሰለፎች ታይተው ነበረ፡፡

መንግስት ይህ ስርዓት መጀመሩ የበረከቱ ጥቅሞች አሉት፣ የነዳጅ ሌብነትም ያስቀራል ያለው አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ 2 ዓመት ቢቆጠርም አሁንም በየ ጊዜው ነዳጅ ደብቀዋል፣ ከዲጂታል ግብይት ውጪ በጀሪካን ጭምር ሲሸጡ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች እንደሚያገኝ ይናገራል፡፡

Comments

Avatar