ሐምሌ 3 2017
ለኢትዮጵያ የትምህርት መውደቅ ምክንያቱ ምንድነው ነው?
በዘርፉ ባለሞያዎች ለዚህ ችግር ምክንያት የተባሉ ነጥቦች ተዘርዝረው ሲቀርቡ ይሰማል፡፡
በትምህርት ዙሪያ የሚሰራ ተቋም አጠናሁት ብሎ ይፋ ባደረገው ውጤት የኢትዮጵያ የት/ት ሥርዓት ተማሪ የተሳሳተውን እንዲያውቅና መልሶ እንዲያርም እድል አለመስጠቱ ትልቁ ችግር ነው ብሏል፡፡
ተማሪዎች በፈተናዎች ወቅት የሚያገኙትን የተሳሳቱ መልሶቻቸውን እንዲያርሙ እድል አለመስጠታቸው እንደ ዋና ችግር ተመልክቼዋለሁ ያለው በዘርፉ ለ20 አመታት ሲሰራ የቆየው ዕርግብ የትምህርት አገልግሎት ይህም የስራ አጥ ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፣ ተማሪዎች ከሌሎች የአለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪነታቸው ዝቅተኛ እንዲሆን እና ሌሎች ችግሮችን አስከትሎብናል ብሏል።
Comments