TRACK
ለአፍሪካ የግብርና ዘርፍ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እንደ ጋራ ኢንቨስትመንት እንጂ እንደ እርዳታ መታየት የለበትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ
ሐምሌ 21 2017
ለአፍሪካ የግብርና ዘርፍ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እንደ ጋራ ኢንቨስትመንት እንጂ እንደ እርዳታ መታየት የለበትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርአት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ ለማሳደግ ከቴክኖሎጂ እስከ ፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅስዋል።
ድጋፉ በዕርዳታ መልክ ሳይሆን በጋራ ኢንቨስትመንት መንፈስ የሚሰጥ ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ከውጭ ጥገኝነት ለመላቀቅ በምርት ዕድገት ላይ እየሰራች ነውም ብለዋል።
Comments