ሐምሌ 10 2017
ምሁራን በጥናትና ምርምር ደረስንበት ብለው የሚያወጡት የጥናት ውጤት ምን ያክል የፖሊሲ ግብዓት ይሆናል?
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ በየጊዜው ምርምር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሲዬሽን በምርምር ስራዎቹ ዙሪያ የሚመክርበት 22ኛ ጉባኤውን ለማድረግ እየተሰናዳ ነው።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ አሶሼሽን በዘንድሮው ዓለም አቀፍ ጉባኤው በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል፣ በኢትዮጵያ የታክስ ሥርዓትና በሌሎች ከ10 በላይ የሚሆኑ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናትና ምርምር እንደሚያቀርብ ሰምተናል።
ጉምቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪዎች የሚሰጡት የምርምር እና የጥናት ወረቀቶችን ፤ መንግስት ተቀብሎ ለፖሊሲ ግብአት ይጠቀምበታል ወይ ተብሎ ይጠየቃል።
Comments