ነሀሴ 7 2017
ወጣቶች በፀጥታና በሰላም ሂደት የሚኖራቸው አቅምና ሚናን በተቋማዊ መንገድ ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
የኢጋንድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ በናይሮቢ ኬኒያ በተከፈተው የኢጋድ የሰላም እና የፀጥታ ኮንፍረንስ ዙሪያ ወጣቶችን የጉዳዩ ባለቤት ማድረግ በተቋማዊ መንገድ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከአፍሪካ አህጉር 70 በመቶው ወጣት በመሆኑ የሰላምና የፀጥታ ጉዳይን ከወጣቶች ውጪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል፡፡
ያለወጣቶች ሰላምን ማሰብ አይቻላም በተመሳሳይ ያለ ሰላም ወጣቶችን ማሰብም ይከብዳል ሲሉ ዶ/ር ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡
ኢጋድ በሰላም እና በፀጥታ ዙሪያ ላለፉት 40 አመታት ሰላምን በአባል ሀገራት ለማምጣት ብዙ ሰርቷል ይሁንና አሁንም የቀራል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
Comments