እስከ ምሽት 3፡30 አልሰራችሁም የተባሉ 366 የንግድ ተቋማት ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
TRACK

እስከ ምሽት 3፡30 አልሰራችሁም የተባሉ 366 የንግድ ተቋማት ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

00:00

ሐምሌ 25 2017

እስከ ምሽት 3፡30 አልሰራችሁም የተባሉ 366 የንግድ ተቋማት ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የምሽት የንግድ ስራን ለማስፈፀም የወጣው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወደተግባር መግባቱ ሲነገር ቆይቶ አሁን ወደ እርምጃ መግባቱን ሰምተናል፡፡

ደምቡን ከሚያስፈፅሙ ቢሮዎች መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ የንግድ ቢሮ የከተማዋ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቅኝት እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በቅኝቱም የንግድ ስራቸውን ለተገልጋዩ ምሽቱን ክፍት አድርገው ማስተናገድ ሲገባቸው ከ3፡30 በፊት ሱቃቸውን በመዝጋት ደምቡን ተላልፈዋል ላላቸው 276 ነጋዴዎች የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

Comments

00:00

litha melamane

awesome. keep it up. have a great weekend. Amen/Allah. greetings from south africa

There is no more content to load