ሐምሌ 4 2017
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 650,000 የአዲስ አበባ ነዋሪ ተጨማሪ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት መቻሉ ተነገረ።
ይህ የተባለው 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርትን ለከተማው ምክር ቤት አባላት ሲያቀርቡ እንዳሉት የከተማው ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮዎችና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ አዲስ አበባ ውስጥ ካለው ነዋሪ ተጨማሪ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ የተቻለው 650,000 ለሚሆነው ብቻ ነው ተብሏል።
Comments