ሐምሌ 2 2017
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የኢትዮጵያን የኤክስፖርት ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ በተለይ የወጪና ገቢ ዕቃን ከማስተላለፍ አልፌ በመንገደኞች የባቡር የትራንስፖርት አገልግሎት ከፍተኛ ማሻሻል አድርጌያለሁ አለ።
አገልግሎት ሰጪው የባቡር የተመደበልኝን ፍጥነት ጨምሬ የምሽት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ልጀምር ነው ብሏል።
የምድር ባቡር ትራንስፖርት ከፍጥነት ባለፈ የደንበኞች ፍላጎትና ጥያቄዎችን ያካተተ አገልግሎት መጀመሩንም ሰምተናል።
የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ከዚህ ቀደም ይነሳበት የነበረው የተዝረከረከ አሰራር እና የቅልጥፍና ማነስ እየፈተሽኩ ውጤት እያመጣሁ እያገኘሁበት ነው ሲል ነግሮናል።
በተለይ የባቡር የትራንስፖርት ክፍሎቹ በንፅህና ያልተያዙ እንደነበሩ የተናገረው ምድር ባበቡሩ፤ አሁን የባቡር ትራንስፖርት ሁሉም ክፍል ንፅህናው ተጠብቆ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ሰምተናል።
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ታሳቢ በማድረግ የመዳረሻ ቁጥሮችን በመጨመር አገልግሎቱን ለቱሪስት መቀበያ ደረጃ ከፍ አድርጌያለሁ ሲል ነግሮናል።
Comments