ነሀሴ 7 2017
በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በድርቅ ምክንያት ከ2,500 በላይ እንስሳት መሞታቸው ተሰማ፡፡
ከ52,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የድርቁ ተጋላጭ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
በወረዳው ድርቁ የተከሰተው ካሉት 24 ቀበሌዎች ውስጥ በ11ዱ እንደሆነ ተነግራል፡፡
በድርቁ ምክንያት የሰዎች ሕይወት ባያልፍም በአካባቢ ያሉ ሰዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየተሰደዱ እንደሆነም ሰምተናል፡፡
የጠለም ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ግዛው ዘነበ በወረዳው ካሉት ቀበሌዎች ውስጥ 11 ቀበሌዎች ላይ ድርቅ መከሰቱን አንስተው ከ11ዱ ውስጥ በአራቱ ቀበሌዎች ላይ ዘግይቶ በከፊል ዝናብ ያገኙ ቢሆንም በ7ቱ ቀበሌዎች ላይ ግን ምንም ዓይነት ዝናብ አላገኙም ብለዋል፡፡
Comments