ሐምሌ 17 2017
ከዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሚመረቁ ተማሪዎች በሁለተኛ ደራጃ ትምህርት ቤቶች ለመስተማር ከፈቀዱ ስልጠና ወስደው መምህር እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ከ2018 ጀምሮ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም በሚል ወደ ስራ ይገባል የተባለው አሰራር የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየውን የመምህራን እጥረት ለመቅረፍ ይረዳል ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር፡፡
ይህ የተባለው የክረምት ልዩ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማሻሻያ ስልጠና ለማስጀመር በማሰብ ከ30 ዩኒቨርሲቲዎች ለተውጣጡ አሰልጣኝ መምህራን እየተሰጠ ያለው ስልጠና በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ድኤታ አየለች እሸቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተፈጥሮ ሳይንስ መምህራን ስልጠና ያልተካፈሉ መምህራን፣ የማህበራዊ ሳይንስ መምህራን፣ የስራና ተግባር ትምህርት መምህራን በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
Comments