00:00
ሐምሌ 29 2017
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ እስላማዊ ቅርሶች እስካሁን ድረስ በተገቢው መንገድ ተደራጅተው እየተዋወቁ አይደለም ተባለ፡፡
ሀገሪቱ ውስጥ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ እስላማዊ ቅርሶች መኖራቸውን የሚጠቀስ ሲሆን ዛሬም በተገቢው መንገድ ትኩረት አላገኙም ተብሏል፡፡
የሰለብሪቲ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ካሳ እስላማዊ ቅርሶችና ሊጎበኙ የሚችሉ መስህቦች የሚል መፅሀፍን አሳትመዋል፡፡
ከአልነጃሺ መስጊድ ጀምሮ እስከ ሃረር ከተማ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ እስላማዊ ቅርሶች መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡
ነገር ግን እነዚህ ቅርሶች ዛሬም ድረስ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ጎብኚዎች በተገቢው መንገድ እንዲተዋወቁ አልተደረገም ብለዋል፡፡
Comments
00:00