00:00
ነሀሴ 7 2017
ህግ ተላልፈዋል ያላቸውን ከ14,000 በላይ ግብር ከፋዮች በገንዘብ መቅጣቱን የገቢዎች ቢሮ ተናገረ።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ይህንን ያለው የግብር አሰባሰቡን ከሌብነት የፀዳ ለማድረግ ያግዙኛል ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች ባስተዋወቀበት መድረክ ነው።
በዚህም የግብር ህጉን ተላላፈዋል የተባሉ 14,220 ግብር ከፋዮች 763 ሚሊዮን 675,000 ብር ተቀጥተዋል ተብሏል።
በገንዘብ ከተቀጡ ግብር ከፋዮች ገሚሱ ማለትም 7,701 ያህሉ ደረሰኝ ባለመቁረጥ እያንዳንዳቸው 100,000 ብር የተቀጡ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ቀሪዎቹ ደግሞ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ባለማደስ፣ ማስታወቂያ ባለመለጠፍ፣ ማሽን ያለ ያለቦታው በማስቀመጥ፣ ለቁጥጥር ባለሙያዎች መረጃ ለመስጠት ባለመተባበር የተቀጡ መሆኑን ቢሮው ተናግሯል።
Comments
00:00