TRACK
በጎረቤት ሡዳን ያለውን ጦርነት በመስጋት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች በአንድ መጠለያ ጣቢያ እንዲሰባሰቡ ተደርጓል ተባለ
ሐምሌ 4 2017
በጎረቤት ሡዳን ያለውን ጦርነት በመስጋት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች በአንድ መጠለያ ጣቢያ እንዲሰባሰቡ ተደርጓል ተባለ።
አሁን ላይ ጦርነቱን ሸሽተው ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር መቀነሱንም ሠምተናል።
በጎረቤት ሡዳን ያለው ጦርነት ያሰጋቸው በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች እና በዚያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያየ ጊዜ ሲገቡ ቆይተዋል።
ጦርነቱን የሰጉ እስከ 47,000 ሰዎች ወደ ክልሉ የገቡበት ጊዜ እንደነበር የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።
Comments
awesome. greetings from cape town