የአዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ከተለያየ የገቢ ምንጭ የሚገኝ ገቢ አንድ ላይ ተጣምሮ ግብር እንዲከፈልበት ያደርጋል ተባለ።
TRACK

የአዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ከተለያየ የገቢ ምንጭ የሚገኝ ገቢ አንድ ላይ ተጣምሮ ግብር እንዲከፈልበት ያደርጋል ተባለ።

Avatar

ሐምሌ 4 2017

የአዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ከተለያየ የገቢ ምንጭ የሚገኝ ገቢ አንድ ላይ ተጣምሮ ግብር እንዲከፈልበት ያደርጋል ተባለ።

ይህም ማለት አንድ ሰው ተቀጣሪ ደመወዝተኛ ሆኖ በተጨማሪ የሚያከራየው ቤት ወይም ሌላ ንግድ ቢኖረው ሶስቱም ገቢው በአንድ ላይ ተሰልቶ ግብር ይከፈልበታል እንደማለት ነው፡፡

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ በተመሳሳይ ሰንጠረዥ ውስጥ ያሉ ብቻ በአንድ የሚጣመሩ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ ግን ከሌላ ዘርፍም ቢሆን አንድ ግለሰብ ተጨማሪ ገቢ ካለው አንድ ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል ተብሏል።

ይህ ለውጥ ግለሰቦች በተበታተነ መንገድ ገቢያቸው ሲሰላ ተደጋጋሚ ከግብር ነፃ የሚሆን ተቀናሽን እያገኙ መንግስት ተገቢውን ገቢ እንዳያገኝ እያደረገ ስለሆነ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ ሰው ከአንድ ምንጭ በሚያገኘው ገቢና ሌላ ሰው ከተለያየ የገቢ ምንጭ በሚያገኘው ተመሳሳይ ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር የተለያየ መሆኑ የፍታዊነት ጥያቄን የሚያስነሳ ስለሆነ እሱን ለማስተካከል ማሻሻያው አስፈልጓል ተብሏለ።

ይህ አሰራር ችግር ሊያስከትል ይችላል የሚል ጥያቄ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተነስቶበታል።

Comments

Avatar