የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የ42 የመንግስት መ/ቤቶች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የ15 መ/ቤቶች ልዩ ልዩ ንብረቶችን ሽያጭ
TRACK

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የ42 የመንግስት መ/ቤቶች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የ15 መ/ቤቶች ልዩ ልዩ ንብረቶችን ሽያጭ

Avatar

ነሀሴ 1 2017

#ቢዝነስ

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት የ42 የመንግስት መ/ቤቶች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የ15 መ/ቤቶች ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ከ275 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ተናገረ፡፡

አገልግሎቱ በ2017 ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ያገኘው ገቢ በ10 ዓመት ውስጥ ከንብረት ሽያጭ ከተሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ ሆኗል ተብሏል፡፡

አንዳንድ ተቋማት በውል ስምምነቱ መሰረት ዕቃ ባለመግዛታቸው ምክንያት በውል አስተዳደር ላይ ቅሬታ እያስከተለ በመሆኑ በአዲሱ ግዥ መመሪያ ላይ ተጠያቂነት ያለበት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ እየሰራሁ ነውም ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ከአቅራቢዎች ለሚቀርቡ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄዎች ምላሽ ያለማግኘት ቅሬታ በመፍጠሩ አቅራቢዎች የሽያጭ ሪፖርታቸውን በወቅቱ እንዲልኩ ክትትል በማድረግ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረኩ ነው ብሏል የመንግስት ግዥ አገልግሎት፡፡

አንዳንድ ተቋማት በውል ስምምነቱ መሰረት ዕቃ ባለመግዛታቸው ምክንያት በውል አስተዳደር ላይ ቅሬታ እያስከተለ በመሆኑ በአዲሱ ግዥ መመሪያ ላይ ተጠያቂነት ያለበት ስርዓት እንዲኖር ጥረት በማድረግ በውይይት ችግሩን በተወሰነ መልኩ ለመፍታት ተሞክሯል ብሏል በዓመታሪ ሪፖርቱ፡፡

Comments

Avatar