ሰኔ 25 2017
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከፍታማ በሆኑ አካባቢዎች ከሚኖሩ ሰዎች 35 ሚሊዮን ያህሉ የሐሩራማ በሽታዎች ስጋት እንዳለባቸው ተነገረ፡፡
ሃሩራማ በሽታዎች ከሚባሉት ውስጥ በተለይ ፖዶኮኖሲስ ወይም ተላላፊ ያልሆነ የዝሆኔ በሽታ ከፍታማ በሆኑና በግብርና ስራ ላይ በተሰማሩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ ትልቅ የህብረተሰብ የጤና ስጋት መሆኑ ተነግሯል፡፡
በጉዳዩ ላይ የሚሰራው ማላሪያ ኮንሰርቴይም የተባለ ድርጅት ህመሙን ለመከላከል እንዲሁም ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች የሚያግዝ ሀፒ ፊት የተባለ ፕሮጀክት ቀርጾ የሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ድርጅቱ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ካላቸው ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና በጉዳዩ ላይ ጥናት ካደረጉት ተቋማት ጋር አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡
ችግሩን ከመሠረቱ መከላከል ላይ በደንብ ካልተሰራበትም በተለይ የችግሩ ተጠቂዎች በአብዛኛው በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በመሆናቸው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያስከትል ነው ተብሏል፡፡
በሽታው የሚከሰተው በዋናነት ከአፈር ጋር በተያያዘ መሆኑንና በተለይ ከፍታ ቦታዎች ቀይ አፈር ያለባቸው አካባቢዎች ያሉት ሚኒራሎች በባዶ እግር ከተረገጡ ወደ ውስጥ በመግባት የጤና ስርዓትን በማዛባት በጊዜ ሂደት እና የእግር እብጠት እንዲያስከትል ያደርጋል የሚሉት በማላሪያ ኮንሰርቲየም ድርጅት (የፖዶኮኖሲስ) ወይም ዝሆኔ በሽታ መከላከል ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት ኃላፊ የሆኑት አቶ እሰይ ባቲሶ ናቸው፡፡
Comments