TRACK
ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ 8,000 እና 9,000 ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ።
ህዳር 25 2018
ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች በፈረሡላ ስምንት ሺህ እና ዘጠኝ ሺህ ብር ይገዛ የነበረ ቡና ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ ላኪዎች እየተቸገሩ ነው ተባለ።
ላኪዎች በዚህ ዋጋ ቡና እየገዙ ለአለም ገበያ ማቅረብ እንደሚከብዳቸው የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል።
አርሶ አደሮች እና ላኪዎች ዋጋውን ከፍ ያደረጉት ወደፊት ይበልጥ ይጨምራል በሚል ግምት እንደሆነም ማህበሩ ጠቅሷል።
ወደ ውጪ ቡና የሚልኩ ነጋዴዎች ከአርሶ አደሮች እና አቅራቢዎች ምርቱን የሚገዙበት ዋጋ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ተናግሯል፡፡
የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ እንዳሉት ቀደም ሲል በፈረሱላ ስምንት ሺህ እና ዘጠኝ ሺህ ብር ከአርሶ አደሮችና አቅራቢዎች ይገዛ የነበረ ቡና አሁን በፈረሱላ እስከ ሃያ ሺህ ብር እየተባለ ነው፡፡
አንድ ፈረሱላ ቡና በሃያ ሺህ ብር ገዝቶ ወደ ለውጪ ገበያ ማቅረብ ለላኪዎች ከባድ ነው ብለዋል፡፡
Comments