ሐምሌ 3 2017
ኢትዮጵያ የወጣቶች ቁጥር የበዛባት መሆኗ አሃዝ እየተጠቀሰ ይነገራል፡፡
ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል በአሁኑ ሰዓት ዋነኛ የሚያሳስበውና በምክክር እንዲፈታለት የሚፈልገው ጥያቄ ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች እና ተፈናቅለው ያሉ ወጣቶችን ጭምር በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ እያደረኩ ነው ብሏል።
ወጣቶቹ ካሲያዟቸው ጥያቄዎች መካከል በወሰን እና በአስተዳደር ያሉ አለመግባባቶች ይፈቱ፣ ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ይኑር፣ መንግስት ለስራ አጥነት መላ ያብጅ፣ በተለይ ወጣቶችን ሰለባ የሚያደርጉ የእርስ በእርስ ግጭቶች በምክክር ይፈቱ የሚሉ እንደሆነም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ነግረውናል።
ህገ መንግስቱን በሚመለከት የተነሱ ጉዳዮች፣ በወሰንና አስተዳደር ያሉ አለመግባባቶች እንዲሁም ግጭቶችን በሚመለከት በወጣቶቹ የተነሱ ጥያቄዎች በሁሉም አካላት በሚባል ደረጃ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተነሱናቸው ያሉት አቶ ጠበቡ በተለይ ስራ አጥነትን፣ ወጣቶችን ሰላባ የሚያደርጉ ግጭቶች እንዲፈቱ፣ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች እንዲከወኑ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል ብለዋል።
ኮሚሽኑ፤ በተለይ ወጣቶች በሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይ እምነት እንዲያሳድሩ በወጣቶች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራዎችን እየሰራሁ ነውም ብሏል።
Comments