ነሀሴ 20 2017
ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮዽያ ገበያ ወጥቼ ወደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ገበያ ውስጥ ለመግባት እቅዴንና ቅድመ ዝግጅቶቼን አጠናቅቄአለሁ አለ።
ኩባንያው በሀገር ውስጥ የዲጅታል አገልግሎት ከመስጠት አልፌ ከኢትዮጵያ ተሻግሬ በአፍሪካና ሌሎች ሀገሮችም ገበያ ለመግባት አቅጃለሁ ብሏል።
ይህን ለማድረግም ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቅቄያለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
ኩባንያው ወደ ሌላ ሀገር ገበያ የምሄደው ገበያውን ለመቀራመት ሳይሆን የዲጅታል መፍትሔዎች ላይ አተኩሬ በምሄድባቸው ሐገሮች መፍትሄ ለማቀበልና ገቢን ለማሳደግ አልሜ ነው ብሏል።
Comments