በሴቶች ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ''ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው የለየናቸው ጉዳዮች ትኩረትም እንዲደረግባቸው''  ሲሉ ጠየቁ
TRACK

በሴቶች ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ''ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው የለየናቸው ጉዳዮች ትኩረትም እንዲደረግባቸው'' ሲሉ ጠየቁ

Avatar

ሐምሌ 17 2017

በሴቶች ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው የለየናቸው ጉዳዮች እንዳይወጡ፣ ትኩረትም እንዲደረግባቸው ሲሉ ጠየቁ፡፡

የሀገራዊ ምክክሩ በበኩሉ የሴቶች ጉዳይ ትኩረት የማያገኝበት ምንም ምክንያት የለም ሲል አስረድቷል፡፡

የሴቶች ማህበራቱ ዋና ዋና እና አንገብጋቢ ናቸው ብለው ለኮሚሽኑ ካስገባቸው አጀንዳዎች መካከል የሰላምና የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የመሬት ባለቤትነት መብት ውስንነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነት ችግር በሴቶች ላይ የሚፈጥረው ጫና ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የገቡት አጀንዳዎች አጀንዳ ብቻ ሆነው እንዳይቀሩ የሁሉም አካላትን ድጋፍ የሚጠይቅ ነው ሲሉ የሴቶቹ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ አሚን መሃመድ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar