ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ህገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው ኢሰመኮ አረጋግጧል
TRACK

ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ህገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው ኢሰመኮ አረጋግጧል

Avatar

ሐምሌ 30 2017

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ ምክንያት በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ህገ ወጥ እስራት፣ ጥቃት፣ ማስፈራራት እና ጣልቃ ገብነት እንደሚፈጸምባቸው የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡

ኮሚሽኑ ባሳለፍነው ሰኞ ባወጣው ሪፖርት በሁለቱ ክልሎች በዳኞች እና በዐቃብያነ ሕግ ላይ ድብደባን ጨምሮ ማስፈራራት እና ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተናግሮ ይህም የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚሸረሽር ስለሆነ የዳኞች ነጻነት እንዲጠበቅ አሳስቧል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በዳኞች እና ዓቃብያነ ሕግ ላይ ለተጠርጣሪዎች ዋስትና ‹‹ፈቅዳችኋል›› ወይም እንዲፈቀድ ‹‹ተባብራችኋል›› በሚል እስራት ድብደባ እና ማዋከብ እንደሚፈጸምባቸው የተናገረው ኢሰመኮ ይህም የሰዎችን የፍትህ ተደራሽነት እንደሚሸረሽር አስረድቷል፡፡

Comments

Avatar