በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ግብር ሲያሸሹ ነበሩ የተባሉ ከ20,000 በላይ የደመወዝ ግብር ከፋዮችን ማስከፈል መቻሉ ተነገረ፡፡
TRACK

በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ግብር ሲያሸሹ ነበሩ የተባሉ ከ20,000 በላይ የደመወዝ ግብር ከፋዮችን ማስከፈል መቻሉ ተነገረ፡፡

Avatar

ሐምሌ 3 2017

በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ግብር ሲያሸሹ ነበሩ የተባሉ ከ20,000 በላይ የደመወዝ ግብር ከፋዮችን ማስከፈል መቻሉ ተነገረ፡፡

ሲያከራክር የነበረው የሆቴሎችና ሌላውም አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (#NGO ) ባለቤቶች ለሰራተኞቻቸው ከሚከፍሉት ደመወዝ የሚቆረጠው የደመወዝ ግብር ጉዳይ በዓመቱ ከፍተኛ ገቢ የተገኘበት ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው፤ ቢሮው አጠናሁት ብሎ ባወጣው መረጃ ሆቴሎችን ጨምሮ አብዛኞቹ አገልግሎት ሰጪዎች ለሰራተኞቻቸው ከሚከፍሉት ደመወዝ ግብር አይከፍሉም ብሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ባስቀመጠው ተመን መሰረት ግብር ሲያስከፍል ቆይቶ የአገልግሎት ዘርፍ የደመወዝ ግብር ከፋዮችን ቁጥር ከ20 ሺህ ወደ 40,000 ሺህ ከፍ በማድረግ በየወሩ ከደሞዝ የሚገኘውን ግብር ከ3.6 ቢሊዮን ወደ 6 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ነግሮናል፡፡

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ የቫት ተመዝጋቢዎችን ለአብነት በመጥቀስ በጥናቱ የተለዩና ከዚህ ቀደም ቫት ተመዝጋቢ ያልነበሩ ግብር ከፋዮችን እንዲመዘገቡ በማድረግ በየወሩ በቫት የሚገኘውን ገቢ ከ860 ሚሊዮን ብር ወደ 2 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል አድርገናልም ብለውናል፡፡

Comments

Avatar