ጥቅምት 11 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ #መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ
TRACK

ጥቅምት 11 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ #መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ

Avatar

ሐምሌ 21 2017

ጥቅምት 11 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ #መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ በርካታ ውድመት ማስከተሉ ይታወሳል።

በሰው እና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

በወቅቱ በስፋት ሲነገሩ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል የከተማዋ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት ገንዘብ ሲደራደሩ፤ ሲቀበሉ ነበር የሚለው ይገኝበታል።

ይሄን ተከትሎም ፖሊስ ለወራት ጉዳዩን ሲከታተል እና ሲመረምረው ቆይቷል።

ፖሊስ በምርመራውም ሲነገር የነበረው ሰራተኞቹ በወቅቱ ገንዘብ ተደራድረዋል፤ ተቀብለዋል የተባለው መረጃ ሃሰት መሆኑን አረጋግጧል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነግሮናል።

Comments

Avatar