ምክክር ኮሚሽንን ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው አብረውት እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተባለ
TRACK

ምክክር ኮሚሽንን ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው አብረውት እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተባለ

Avatar

ሐምሌ 21 2017

በኢትዮጵያ ካሉ ወደ 5,000 ገደማ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ተልዕኮና ዓላማ ተረድተው አብረውት እየሰሩ ያሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

ይህን ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ነው፡፡

ምክር ቤቱም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የኮሚሽኑን ዓላማ ካለመረዳትና በፋይናንስ እጥረት ምክንያት በሚፈለገው ልክ በአገራዊ ምክክሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

በምክሩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚፈለገው ደረጃ በንቃት አለመሳተፍ እንደሚያሳስበው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተናግሯል፡፡

Comments

Avatar