መንግስት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲሉ በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ጠየቁ፡፡
TRACK

መንግስት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲሉ በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ጠየቁ፡፡

Avatar

ነሀሴ 6 2017

መንግስት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲሉ በጎንደር ቀበሮ ሜዳ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ጠየቁ፡፡

እነዚህ ከ2,000 በላይ የሚሆኑ #ተፈናቃዮች በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በቀበሮ ሜዳ መኖር ከጀመሩ አምስት አመት እንደሆናቸው ነግረውናል፡፡

ለአማራ ክልል መንግስት ከተቻለ የምንሰፍርበት ቦታ ይሰጠን አሊያም ደግሞ ማቋቋሚያ ተሰጥቶን ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሄደን የምንሰራበት መላ ይፈጠርልን ብለን ብንጠይቅም መልስ ሊሰጠን ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል፡፡

ጥናት ተደርጎ 97 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ሌላ ቦታ ተሰጥቷቸው መስፈር እንደሚፈልጉ ቢናገሩም ተግባራዊ የተደረገ ነገር የለም ይላሉ ተፈናቃዮች፡፡

Comments

Avatar