TRACK
ከረጃጅም ፅሁፎች ይልቅ አጠር አጠር ወዳሉና ሰዓታት ከሚፈጁ ቃለ መጠይቆች ወይም ንግግሮች ይልቅ በሴኮንድ ግፋ ቢል በደቂቃ እድሜ ወደ ሚያልቁት ማዘንበል
ነሀሴ 30 2017
ከረጃጅም ፅሁፎች ይልቅ አጠር አጠር ወዳሉና ሰዓታት ከሚፈጁ ቃለ መጠይቆች ወይም ንግግሮች ይልቅ በሴኮንድ ግፋ ቢል በደቂቃ እድሜ ወደ ሚያልቁት ማዘንበል በስፋት እየተስተዋለ መሆኑ ይነገራል፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ቲክቶክ ዩቲዩብ ያሉ መተግበሪያዎችና የኢንተርኔት መስፋፋት አግዞታል፡፡
ሰዎች ረጃጅም ምስሎችን ከማየት፣ረዘም ያሉ ንግግሮችን ከመስማት፣ብዙ ገፅ የያዙ መፅሐፍትን ከማገላበጥ ርቀው የዘመኑ ቴክኖሎጂ ወደ አመጣው ጊዜ ቆጣቢና አጫጭር ነገሮች ላይ ማተኮራቸው ጥቅሙ እንዳለ ሆኖ ጉዳቱም ግን በዚያው ልክ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡
በቅርቡ በተደረገ ጥናት ሰዎች አጫጭር ቪዲዮዎችን አብዝተው በማየታቸው ብቻ አዕምሮአቸው አንድ ነገር ላይ ትኩረት የማድረግ አቅሙን ወደ 47 ሰከንድ በማውረድ ትዕግስት የለሽ እና ችኩል ትውልድ እየፈጠረ ነው ተብሏል፡፡
አቶ ቴዎድሮስ ጌትዬ የሰዎች ስነ ባህሪ ጥናት ባለሞያ ናቸው፡፡ ባለሞያው ሰዎች በአጭር ቪድዮ የስነ ልቦና ተፅዕኖ ስር መግባታቸው፣ ኑሮአቸው ላይም ትኩረታቸውን በስራ ሂደት ላይ ሳይሆን በመጨረሻው ውጤት ላይ ብቻ በማድረግ ለለውጥ ሁሌም አቋራጭ መንገድን እንዲመርጡ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ ያሳድርባቸዋል ይላሉ፡፡
Comments