TRACK
የባህላዊ ህክምና ዘርፍ ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሀገር በቀል ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ዕጽዋት ከመጥፋት መታደግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
00:00
ሐምሌ 24 2017
በኢትዮጵያ ከዘመናዊ ህክምና ባልተናነሰ የሚሠራበት የባህላዊ ህክምና ዘርፍ ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሀገር በቀል ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ዕጽዋት ከመጥፋት መታደግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡
በብዛት በሚበቅሉባቸው አካባቢዎች ላይ መመናመንና የመጥፋት ስጋት ያለባቸው ሀገር በቀል እጽዋት መኖራቸውን የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ተናግሯል፡፡
ሀገር በቀል ሆነው በተለይ በኢትዮጵያ የአየር ፀባይ የሚበቅሉ እጽዋት ቁጥር ተለይተው በሚበቅሉባቸው አካባቢዎች ላይ እየተመናመኑ መምጣታቸውንና ለመጥፋትም እንደተቃረቡ የለየናቸው ዝርያዎች አሉ የሚሉት በኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት የደንና የግጦሽ ብዝሃ ህይወት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ አበራ ስዩም ናቸው፡፡
እየተመናመኑ ያሉ ሀገር በቀል እጽዋት የተለዩ አሉ የሚሉት አቶ አበራ የተመናመኑ ስንል ከየአካባቢያቸው የተመናመኑ እና ለመጥፋት የተቃረቡ ዝርያዎች ናቸው፤ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጡ ለምሳሌ የኰሶ ዛፍ፣ ጥቁር እንጨት እና ቀረሮ ሀገር በቀል ከመሆናቸው በተጨማሪ ለመድኃኒትነት የሚውሉም ናቸው ብለዋል፡፡
Comments
00:00
awesome. have a nice day. Amen/Allah. greetings from south africa