00:00
ሐምሌ 1 2017
በኢትዮጵያ በስፋት አገልግሎት የሚሰጡ የግኙነት ሶፍትዌሮችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ በተሰሩት ለመተካት በሂደት ላይ መሆኑን ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ( #INSA ) ተናገረ፡፡
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደሰማነው ከሆነ ኢሜይል፣ ቴልግራምና ዋትሳፕን ጨምሮ ሌሎችም አለም አቀፍ ሶፍትዌሮች በሃገር ውስጥ በሚሰሩ ሶፍትዌሮች ተተክተው በመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት ችለዋል፡፡
ኢንሳ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ ከምከውናቸው ስራዎች በተጨማሪ ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ ሶፍትዌሮችን እያበለፀግኩ አንዳንዶቹንም እየተካሁ ነው ብሏል፡፡
ይህንን ማድረግ ያስፈለገው የውጪዎቹን የመገናኛ ዘዴዎችን መጠቀም እንደ ሃገር ጥብቅ የሆኑ መረጃዎች ሳይቀሩ እንዲመዘበሩ ምክንያት ስለሚሆን ነው ያሉን የኢንሳ የሽያጭ ባለሙያው አቶ እሸቱ፤ በኢንሳ የተሰራው ’’ኤርጋሜይል’’ የተሰኘው ሶፍትዌር ኢ-ሜይልን ተክቶ ተቋማቸውን ጨምሮ በሌሎችም የመንግስት ተቋማት እየተሰራበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
Comments
00:00