በደብረ ብርሃን የነበሩና ወደ ቀያቸው የተመለሱ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቡሰዮ ወረዳ ያሉ ተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦት ተቋርጦብናል አሉ፡፡
TRACK

በደብረ ብርሃን የነበሩና ወደ ቀያቸው የተመለሱ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቡሰዮ ወረዳ ያሉ ተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦት ተቋርጦብናል አሉ፡፡

Avatar

ነሀሴ 16 2017

በደብረ ብርሃን የነበሩና ወደ ቀያቸው የተመለሱ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቡሰዮ ወረዳ ያሉ ተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦት ተቋርጦብናል አሉ፡፡

በወረዳው 107 የሚጠጉ አባወራዎችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ምግብ እና ሌሎች እርዳታዎችን ሲያደርግላቸው እንደቆየ እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ እርሻ መሬታችሁ እና ቤታችሁ ትመለሳላችሁ ተብሎ ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር ተፈናቃዮቹ ነግረውናል፡፡

ነገር ግን ወደ ጉቡሰዮ ወረዳ ከመጣን 1 አመት ከ8 ወር ገደማ ሆኖናል፤ ያለነውም በኪራይ ቤት ነው ይላሉ፡፡

በተጨማሪም እስከ ቅርብ ወራት ድረስ መንግስት የምግብ እርዳታ እያቀርብልን ነበር ያሉት ተፈናቃዮቹ አሁን ግን እርዳታው ከተቋረጠብን ወራት አልፎናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

Comments

Avatar