የተሻሻለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ በማህበረሰቡ ቅሬታ እየፈጠረ ነው
TRACK

የተሻሻለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ በማህበረሰቡ ቅሬታ እየፈጠረ ነው

Avatar

ነሀሴ 19 2017

2017 ዓ.ም ከመስከረም ጀምሮ የተሻሻለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ በማህበረሰቡ ቅሬታ እየፈጠረ ነው።

ከወርሃ መስከረም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ለቀጣይ 4 ዓመታት በየሶስት ወር ተከፋፍሎ በ16 ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መናገሩ ይታወቃል፡፡

ይህም አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የሚጠቀሙ ደንበኞችን እንዳይጎዳ፣ የኑሮ ደረጃን ያገናዘበና ድጎማን መሰረት ያደረገ ማስተካከያ እንዳደረገም በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምተናል።

ነገር ግን ይህ ጭማሬ በብዙዎች የአገልግሎቱ ደንበኞች ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎቹ ነግረውናል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩል ተግባራዊ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ግሽበትን እንዳያባብስ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ደንበኞች የመክፈል አቅም ያገናዘበ እና ድጎማ የሚያርግ ነው ብሏል፡፡

Comments

Avatar