ታክሲዎች ምሽት ላይ የሚያደርጉት ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪ አላስፈላጊ ወጪ እያስወጣቸው እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውናል
TRACK

ታክሲዎች ምሽት ላይ የሚያደርጉት ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪ አላስፈላጊ ወጪ እያስወጣቸው እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውናል

Avatar

ጳጉሜ 3 2017

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች ምሽት ላይ የሚያደርጉት ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪ አላስፈላጊ ወጪ እያስወጣቸው እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውናል፡፡

የስምሪት መስመሩን መደበኛ ታሪፍ በእጥፍ የሚያስከፍሉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዳሉም ሰምተናል፡፡

ያነጋገርናቸው የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች በበኩላቸው እንዳንድ የስምሪት ተቆጣጣሪዎች ያለፍላጎታችን አምሽተን እድንሰራ ያስገድዱናል፤ ከመሸ ደግሞ ጭነን ስንሄድ እንጂ ስንመለስ ተሳፋሪ ስለማናገኝ የተወሰነ ጭማሪ እናደርጋለን ያም ቢሆን እንደሚባለው የተጋነነ አይደለም ብለውናል፡፡

Comments

Avatar