ሀገር የሚገነባው በሰው ነው፤ ሰው ላይ ሲሰራ ብቻ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
TRACK

ሀገር የሚገነባው በሰው ነው፤ ሰው ላይ ሲሰራ ብቻ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

Avatar

#ምጣኔ_ሐብት

ዛሬ ህፃናት የሚውሉበት መሰረት የሚጥሉበት መዋያ በየሰፈር መንደሩ እና ጉራንጉሩ መሆኑ ትምህርት ከንግድ አለመላቀቁን እና ከያዋጣኛል፣ አያዋጣኝም ማዕዘን አለመላቀቁን ያስረዳል።

ይህ በመሆኑ በእርግጥ የ ኋላ ኋላ ድካሙ የማይመለስ እና የማይቋረጥ ይሆናል።

ከታች ከመሰረቱ የተነደፈ፣ የተሰራ በሥርዓት በወግና በያገባኛል ስሜት መመሪያና ደንብ የታነፀ መሰረት ሁሉ ለዘመናት ይፀናል።

አንድን ጉዳይ ለይድረስ ይድረስ ለጊዜያዊ የችግሩ መፍቻ ብቻ በማሰብ ማከናወን ሥራው ወደኋላ ይመልሳል።

ይህ ክፉ ልማድ ዛሬም አብሮ እንዳይጓዝ የሌሎች ሀገሮችን ልምድ ከስር ከመሰረቱ በማጥናት በሀገር ቤት ባህልና ወግ ጋር ማስማማት ይጠይቃል።

Comments

Avatar