ሐምሌ 30 2017
ኢትዮጵያ ውስጥ በግል ከተያዙ ግዙፍና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሴቶች ተሳትፎ 25 በመቶ መድረሱን ጥናት አሳየ፡፡
ሴቶች በሃላፊነት ቦታ ላይ ደግሞ ያላቸው ድርሻ አንድ አምስተኛ መሆኑን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያደረገው ጥናት አሳይቷል፡፡
የተጠቀሱትና ሌሎችም የጥናቱ ውጤቶች ሴቶች በስራ ላይ ያላቸው ተሳትፎ እያደገ መሆኑን ቢያሳይም ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር ደመወዛቸው በ25 በመቶ ያንሳል ተብሏል፡፡
ሴቶች በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያላቸው ተሳትፎ ፤ የሚመሯችው ድርጅቶች ውጤታማነትና የሚከፈላቸው ደመወዝ በጥናቱ ከተዳሰሱ ጉዳዮች መካከል ናቸው።
የጥናቱ ውጤቱ እንደ ሚለው እንደ ንግድ ባሉ የአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ውጤታማ ሆነው ተገኝተዋል።
Comments